Fana: At a Speed of Life!

በቆላማ አካባቢዎች ያሉ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ኑሮ የሚያሻሽሉ ፕሮጀክቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – አብርሃም በላይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቆላማ አካባቢዎች ያሉ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ኑሮ የሚያሻሽሉ ፕሮጀክቶች ትግበራ ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፡፡

የቆላማ አከባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አብይ ኮሚቴ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል፡፡

በተጨማሪም በፕሮጀክቱ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ በመወያየት 28 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በጀት ማጽደቁን ሚኒስትሩ አመልክተዋል፡፡

በቆላማ አካባቢዎች ልማትን ለማፋጠንና የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ የተናበበና የተቀናጀ ስራ እንዲሁም የአርብቶ አደሩን ህይወት የሚቀይሩ ፕሮጀክቶችን መተግበር እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ በቆላማ አካባቢዎቿ ያሏትን የመሬት፣ ውሃ፣ የእንስሳትና ሌሎች ሀብቶችን ጥቅም ላይ በማዋል የአርብቶ አደሮችን ኑሮ የሚያሻሽሉና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን የሚያጎለብቱ ስትራቴጂያዊ ፕሮጀክቶችን መተግበር ያስፈልጋል ነው ያሉት።

በቀጣይም በተናበበና በተናጀ የቆላማ አከባቢ ልማት የዜጎችን ኑሮ የማሻሻል ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የቆላማ አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በ424 ሚሊየን ዶላር በጀት በሰባት ክልሎችና በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ 120 ወረዳዎች ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.