በምዕራብ ጉጂ ዞን በአሸባሪው ሸኔ ላይ የተጠናከረ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ያለው ጥምር የጸጥታ ኃይል በአሸባሪው ሸኔ ላይ የተጠናከረ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
የመከላከያ ሰራዊት የ94 ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ታደሰ ጉተማ÷ ጥምር የጸጥታ ኃይሉ ሽብርተኛው ሸኔን ለማጥፋት እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ጥምር የጸጥታ ኃይሉ በምዕራብ ጉጂ ዞን ተበታትኖ የሚገኘውን የሽብር ቡድን ጠራርጎ ለማስወጣት በብቁ ቁመና ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው÷ የቡድኑን እንቅስቃሴ ለመገደብ በዞኑ በሕዝብ ተሳትፎ የተጀመረው የሕግ ማስከበር ሥራ ውጤት እያስገኘ ነው ብለዋል።
የምዕራብ ጉጂ ዞን ገላን ወረዳ ነዋሪዎች በበኩላቸው÷ የመንግስት ጥምር የጸጥታ ኃይል በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየወሰደ ላለው እርምጃ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
የወረዳው ነዋሪዎች በዞኑ ቶሬ ከተማ ከፌደራል፣ ከክልልና ከዞን ጥምር የጸጥታ ኃይል አመራሮች ጋርኃደረጉት ውይይት÷ ሽብርተኛው ሸኔ ከማንም በላይ የጉጂ ኦሮሞ ጠላት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በላይ ጊዜ ሊሰጠው እንደማይገባም በአጽንኦት መናገራቸው ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ለሸኔ ስንቅና ትጥቅ የሚያቀብሉ የሽብር ቡድኑ ደጋፊዎችን በማጋለጥ የሕግ የበላይነት እንዲከበር የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!