ባለፈው በጀት አመት ከ336 ቢሊየን ብር በላይ ተሰብስቧል- ሚኒስቴሩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 በጀት ዓመት 336 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ የ2014 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸሙን እንዲሁም የ2015 በጀት ዓመት እቅዱን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ አማካሪዎች፣ ዳይሬክተሮች እና የየቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጆች በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል፡፡
በመድረኩ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው÷ በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ከታቀደው 360 ቢሊየን ብር ውስጥ 336 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
በዚህም የእቅዱን 93 ነጥብ 53 በመቶ ማሳካት መቻሉን ጠቅሰው፥ ከ2013 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የ20 ነጥብ 7 በመቶ ወይም የ57 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
መድረኩ በ2014 በጀት ዓመት የታዩ ጠንካራ ስራዎችን ለማስቀጠል፣ በድክመት የሚታዩትን ለማስተካከል እና ለ2015 በጀት ዓመትም እንደግብዓት ለመውሰድ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ መነገሩን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!