Fana: At a Speed of Life!

 ክሪስታል ፓላስ በዩሮፓ ሊግ እንደማይሳተፍ ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዙ ክለብ ክሪስታል ፓላስ በሚቀጥለው የውድደር ዓመት በዩሮፓ ሊግ እንደማይሳተፍ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አስታወቀ፡፡

ንስሮች በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ ማንቼስተር ሲቲን በማሸነፍ ሻምፒዮን የሆኑ ሲሆን በዩሮፓ ሊግ የሚሳተፉበትን እድልም አግኝተው ነበር፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ መድረክ የመሳተፍ እድል አግኝቶ የነበረው  ክሪስታል ፓላስ በተመሳሳይ ክለብ ባለቤትነት ህግ ጋር በተያያዘ ከዩሮፓ ሊግ ውጪ ሆኗል።

የዩሮፓ ሊግ ተሳታፊው ኦሎምፒክ ሊዮኑ ባለቤት ጆን ቴክስተር በክሪስታል ፓላስ ድርሻ ያላቸው ሲሆን በዚህም ንስሮቹ ከተመሳሳይ የክለብ ባለቤትነት ጋር በተያያዘ የዩሮፓ ሊግ ተሳታፊነታቸውን መነጠቃቸውን ማህበሩ ገልጿል።

የኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊው ክሪስታል ፓላስ በቀጣይ በኮንፈረንስ ሊግ የሚሳተፍ ሲሆን  ኖቲንግሀም ፎረስት በበኩሉ በዩሮፓ ሊግ እንደሚሳተፍ አረጋግጧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.