በአፋር ክልል ለ520 ሺህ ዜጎች የአስቸኳይ ምግብ እርዳታ ተሰራጨ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ምግብ ፕሮግራም በአፋር ክልል ችግር ውስጥ ለሚገኙ 520 ሺህ ዜጎች አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ማሰራጨቱን አስታውቋል፡፡
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተከሰተው ግጭት ሳቢያ በአፋር ክልል ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚያሰራጨውን አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ማጠናቀቁን አስታውቋል፡
ፕሮግራሙ በክልሉ በሚገኙ 14 ወረዳዎች ባሰራጨው የሰብዓዊ እርዳታ 520 ሺህ የሚሆኑ ዜጎችን ተደራሽ ማድረግ መቻሉ አመላክቷል፡፡
በዚህም የሰብዓዊ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ዜጎች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑትን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!