Fana: At a Speed of Life!

የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ሒደት በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል – ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ሒደት በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) አዲሱን የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ሒደትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ስዩም መኮንን፣ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ አቶ ደሳለኝ አስራደ እና ሌሎች የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የድልድዩ ግንባታ ሒደት በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ድህንነትን ማጥፋትና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ የሚቻለው በቅድሚያ የመሰረተ ልማት አውታሮችን ተደራሽ ማድረግ ስንችል ነው ብለዋል።

ድልድዩ የህዝባችንን ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ ጉልህ ድርሻ አለው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ ግንባታውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በጀት እየተገነባ የሚገኘው አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በነባሩ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ላይ የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ የሚቀርፍ ነው ተብሏል።

አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ የፊታችን ሰኔ ወር መጨረሻ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.