Fana: At a Speed of Life!

በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር በአሶሳ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ መሪነት በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ  ክልል በአሶሳ ከተማ ተጀምሯል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻዲሊ ሀሰን፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ይስሀቅ፣የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና ርዕዮተ አለም ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዛዲግ አብርሀ፣የወጣቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወጣት  አክሊሉ ታደሰ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

ከ8 ሚሊየን በላይ በላይ ወጣቶች ተሳታፊ ይሆኑበታል ተብሎ በሚጠበቀው በዘንድሮው የክረምት በጎ ፍቃድ እንቅስቃሴ ከ400 ሚሊየን በላይ ችግኞች በመትከል፣በሺዎች የሚቆጠሩ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ እንዲሁም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዩኒት ደሞችን በደም ልገሳ ለማሰባሰብ እቅድ ተይዟል።

መላው የሀገሪቱ  ወጣቶችም አላማው ግቡን እንዲመታ ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ መቅረቡን ከብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.