Fana: At a Speed of Life!

የምክክር ኮሚሽን በተለያዩ አውሮፓ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አጀንዳዎችን ተረከበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በስዊዲን፣ በኖርዲክ እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተለዩ አጀንዳዎችን ተረክቧል፡፡
ኮሚሽኑ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አጀንዳዎችን ያሰባሰበበት እና የሀገራዊ ምክክር ተሳታፊዎችን ያስመረጠበት መድረክ በስዊዲን ስቶክሆልም ዛሬ አካሂዷል፡፡
በመድረኩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን የወከሉ ተሳታፊዎች አጀንዳዎቻቸውን በተለያዩ ቡድኖች አጠናቅረውና አደራጅተው ለኮሚሽኑ አስረክበዋል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ በሚካሄደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ወኪሎችን መርጠዋል።
የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገ/ስላሴ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ፤ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በምክክሩ ላደረጉት ንቁ ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች ከሌሎች አጀንዳዎች ጋር በኮሚሽኑ ምክር ቤት ተቀርፀው ለሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ግብዓት እንደሚሆኑም አስረድተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.