Fana: At a Speed of Life!

በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተያዘ ማዳበሪያ ለወጣቶችና አርሶ አደሮች እየተሰራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ከተያዘ 453 ኩንታል ማዳበሪያ ከፊሉ በእርሻ ዘርፍ ሥራ ለተፈጠረላቸው ወጣቶች እና አርሶ አደሮች እየተላለፈ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ከፊሉ ማዳበሪያ ደግሞ በሕግ አግባብ ውሳኔ እስከሚሰጠው እየተጠበቀ መሆኑን የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ምክትል እና የግብርና ግብዓት ዘርፍ ኃላፊ በላይነህ ባራሞ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ከሕገ-ወጥ ማዳበሪያ ዝውውር ጋር በተያያዘም 12 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው በሕግ እየታየ መሆኑን ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለጹት፡፡

369 ኤን ፒ ኤስ እና 84 ኩንታል ዩሪያ ማዳበሪያ የተያዘው በክልሉ በሚገኙ በተለየዩ ወረዳዎች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.