አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አብርሆት ቤተ -መጻሕፍት የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ 24 ሰዓት ማሳደጉን አስታውቋል፡፡
የቤተ-መጻሕፍቱ ዋና ዳይሬክተር ውብአየሁ ማሞ(ኢ/ር)÷ቤተ-መጻሕፍቱ ከሕዳር 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ምሽቱ ስድስት ሰዓት አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየ አንስተዋል፡፡
ከዛሬው ዕለት ጀምሮም የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ነው ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡
የቤተ-መጻሕፍቱ አገልግሎት ፈላጊ ቁጥር የአገልግሎት ሰዓቱን ለማሻሻል ምክንያት እንደሆነም አመላክተዋል።
ቤተ-መጻሕፍቱ በቀን ከ15 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በሌላ በኩል ቁጥር ሁለት የአብርሆት-ቤተ-መጻሕፍት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሊገነባ መሆኑ ተገልጿል።
በሜሮን ሙሉጌታ