የደቡብ ኢትዮጽያ ክልል ቀጣዩን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ያስተናግዳል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጽያ ክልል ቀጣዩን 19ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በአርባ ምንጭ ከተማ እንደሚያስተናግድ ይፋ ተደርጓል።
በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን “ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሯል፡፡
እንዲሁም በዚሁ ወቅት የሶማሌ ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫን ከሲዳማ ክልል ተረክቧል።
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫን ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) እና ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እጅ ተቀብለዋል።
በመላኩ ገድፍ