Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና የሶማሊላንድ ስምምነት ለቀጣናዊ ውህደት ጉልህ ሚና አለው – አምባሳደር ጀማል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው ስምምነት ለቀጣናዊ ውህደት፣ ሰላም እና ብልፅግና ጉልህ ሚና አለው ሲሉ በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት እውን የሚያደርግ፣ የባህር በር አማራጮችን የሚያሰፋ፣ የሁለቱን ወገኖች የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ፣ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ሠነድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሂ አብዲ መፈራረማቸው ይታወቃል።

አምባሳደር ጀማል የተደረሰውን ስምምንት አስመልክተው በሰጡት መግለጫ÷ ስምምነቱ የኢትዮጵያ መንግስት የህዝቡን የረጅም ጊዜ ጥያቄ እና ምኞት የመለሰ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ስምምነቱ የኢትዮጵያ መንግስት ለቀጣናዊ ውህደት፣ ለጋራ ሰላም እና ደህንነት እንዲሁም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ያለውን ጠንካራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ እውነተኛ ነጸብራቅ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለጅቡቲ፣ ኬንያ እና ሱዳን ሐይል እየላከች ነው ያሉት አምባሳደሩ÷ ሀገሪቱ ሃብቶቿን በማካፈል ከወንድማማች ጎረቤት ሀገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት እየፈጠረች መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

አሁን የተፈረመው የስምምነት ሠነድ ከግብ እንዲደረስ ጥረት ላደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለሶማሊላንዱ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.