Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ፈቃድ መስጠት ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከየካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ፈቃድ መስጠት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ÷ ድርጅቱ ከተቋቋመ ጊዜ አንስቶ ራሱን በማደራጀት የሕግ ማዕቀፍ ሲያዘጋጅ መቆየቱን አንስተዋል፡፡

አሁን ላይም የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ በማዘጋጀት ወደ ሥራ መግባቱን ነው የገለጹት፡፡

በዚህ መሰረትም በዘርፉ ሥራ ላይ የሚገኙ አካላት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ መመዝገብ እንደሚችሉ አስታውቀዋል፡፡

ባለስልጣኑ 15 አዳዲስ ፈቃዶች መስጠት እንደሚጀምርም ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡

በኢትዮጵያለመጀመሪያ ጊዜ ለኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ መስጠት እንደሚጀመር ጠቁመው÷5 የመንግስት የልማት ድርጅቶችም በዚህ ማዕቀፍ ለመካተት ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ሶስት ትላልቅ የውጭ ኢንቨስትመንት ባንኮች መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እንደተሰጣቸው አስረድተዋል፡፡

የውጭ ኢንቨስትመንት ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ መግባትም ገበያው ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ አስገንዝበዋል።

በዘመን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.