በቡሌ ሆራ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) በኦሮሚያ ክልል ቡሌ ሆራ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ ፡፡
በውይይቱ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በውይይት መድረኩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከሕብረተሰቡ ጋር መክረዋል፡፡
መድረኩ” ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና “በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው፡፡
በማርታ ጌታቸውና ለሊሴ ተስፋዬ