ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከአማራ ክልል ዞኖች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሁሉም የአማራ ክልል ዞኖች ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ከሁሉም የክልሉ ዞኖች የተወጣጡ ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡
ዛሬ የተካሄደው ውይይትም ባለፈው ሳምንት በክልሉ የተደረጉ ውይይቶች ማጠቃለያ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ ተወካዮችም የተለያዩ ጉዳዮችን ማንሳታቸው ተገልጿል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩም በክልሉ የሰላም እና ፀጥታን አስፈላጊነት አፅንዖት በመስጠት÷ እየተከናወኑ ባሉ የልማት ፕሮጀክቶች ሥራ ላይ ያተኮረ ምላሽ ሰጥተዋል።
ከአማራ ክልል ተወክለው በውይይቱ የተሳተፉ አካላትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እያከናወኗቸው ላሉ ተግባራት ምስጋና አቅርበው ስጦታ አበርክተውላቸዋል።