በአደጋዎች የተጎዱ ዜጎችን የሚረዳ የ18 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀት ትግበራ ላይ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአደጋዎች የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎችን በዘላቂ መፍትሄ አይበገሬነትን ለማጠናከር የሚያስችል የፕሮጀት ትግበራ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የምክክር መድረኩ በኢትዮጵያ መንግስት እና በዓለም አቀፉ የፍልሰት ተቋም (አይኦኤም) አዘጋጅነት ነው የተካሄደው፡፡
ፕሮጀክቱ በዓለም አቀፉ የፍልሰት ተቋም፣ በዓለም የምግብና እርሻ ድርጅትና ዩኤን ሃቢታት የሚተገበር መሆኑን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
18 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የተመደበለት ፕሮጀክቱ÷ የአራት ዓመታት ቆይታ እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡
ፕሮጀክቱ 54 ሺህ 396 ተፈናቃዮችን፣ ከስደት ተመላሾችንና ተቀባይ ማህበረሰቦችን ተጠቃሚ እንደሚደረግ ነው የተገለጸው፡፡
በምክክሩ ባለድርሻ አካላት በባለቤትነት ለውጤት እንዲንቀሳቀሱና አስተባባሪ ኮሚቴውም በንቃት እንዲሰራ መግባባት ላይ መደረሱ ተጠቅሷል፡፡
134