Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የበለጠ እንደምታጠናክር አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና እና ኢትዮጵያ የኢትዮጵያና ቻይና ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የበለጠ እንደሚጠናከር በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩአን ገለጹ፡፡

ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩአን ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩአን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ የቻይና እና ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የበለጠ እንደሚጠናከር ገልጸዋል፡፡

ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ቻይና እና ኢትዮጵያ ትብብራቸው ከሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ ስትራቴጂካዊ የትብብር አጋርነት ወደ ‘ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት’ መቀየሩን ማስታወቃቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.