Fana: At a Speed of Life!

የገጠሙንን ፈተናዎች ማለፍ የሚቻለው ሁላችንም ተቀራራቢ አፈፃፀም ላይ ስንገኝ ነው – አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገጠሙንን ውስብስብ ፈተናዎች ማለፍና የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ከግብ ማድረስ የሚቻለው ሁላችንም ተቀራራቢ አስተሳሰብና አፈፃፀም ላይ ስንገኝ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ አብዱልከሪም መንግስቱ ገለጹ፡፡

የደሴ ከተማ አስተዳደር መንግስት ሰራተኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው፡፡

በውይይቱ የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን አጋዥ ከመሆን ባለፈ ለልማትና ሰላም መረጋገጥ ትልቁን ድርሻ የሚወጣው የመንግስት ሰራተኛው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

አቶ አብዱልከሪም÷የኢትዮጵያን የልማት እና ሰላም እንቅፋቶች መፍታት የሚቻለው የውጭ ተጋላጭነትን ከመከላከል ባሻገር ወንድማማችነትን ማጠናከር ሲቻል መሆኑን አንስተዋል።

ከህዝቡ ጋር በመተባበር አመራሩና የመንግስት ሰራተኛው ባከናወናቸው ተግባራት ደሴ ከተማ አንፃራዊ መረጋጋት እንዲኖር ማድረጉ ተጠቅሷል፡፡

የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው፥ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ከግብ እንዲደርሱ በየክፍለ ከተሞች ያሉ የመንግስት ሰራተኞች ሚና ቀላል አይደለም ብለዋል።

ነዋሪውን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የመንግስት ሰራተኞችን ጭምር እየፈተነ ላለው የኑሮ ውድነት ምንጩ ሰላም ማጣት መሆኑን ጠቁመው÷ ለመፍትሔው በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በእለኒ ተሰማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.