የአፍሪካ መሪዎች በመዲናዋ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ መሪዎች በአዲስ አበባ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡
የአፍሪካ መሪዎች የትውልድ ግንባታ ስራዎችን ጨምሮ በአዲስ አበባ በተሰሩ ዋና ዋና የልማት ስራዎች ዙሪያ ልምድ ለመካፈል አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ለልምድ ልውውጡ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ መሪዎች እና ከተለያዩ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች የመጡ እንግዶችን ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ ተቀብለው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በማስጎብኘት ላይ ይገኛሉ።
በልምድ ልውውጥ መርሐግብሩ ላይ የክልሎች ምክትል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉ ከከተማው ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡