ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በስሩ ከሚተዳደሩ ኩባንያዎች ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ጋር ተወያዩ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ዛሬ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በስሩ ከሚተዳደሩ ኩባንያዎች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ተወያይተናል ብለዋል።
በዚህም በኩባንያዎች መፈፀም ስላለባቸው የኦዲት፣ የትርፍ ድርሻ ክፍያ፣ ከሆልዲንጉ ጋር ባለው የስራ ግንኙነት የነበሩ መልካም አፈፃፀሞች እንዲሁም ፈጥነን በጋራ መፍታትና መሻገር ስለሚገቡን ተግዳሮቶች ምክክር አድርገን ተግባብተናል ሲሉ ገልጸዋል።