ሚኒስቴሩ ለጎፋ ዞን 6 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ከ6 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብሩ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን÷ 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመተው ደግሞ በአይነት መሆኑ ተገልጿል።
የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም በአደጋው በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸው÷ድጋፉን ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ አስረክበዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀጣይ በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋምና ለመደገፍ የተለያዩ አካላትን በማስተባበር የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንደሚያደርግ መናገራቸውንም የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡