Fana: At a Speed of Life!

በግራንድ ፕሪ ውድድር የተሳተፉ ስመ ጥር አትሌቶች በአዲስ አበባ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ በግራንድ ፕሪ ውድድር የተሳተፉ ስመ ጥር ዓለም አቀፍ አትሌቶች በአዲስ አበባ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ አትሌቶቹ የአዲስ ስፖርት ፓርክ፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዚህ ወቅት አትሌቶቹ በጉብኝታቸው ታሪክንና የከተማ ውበትን መመልከት መቻላቸውን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ልማትና በከተማዋ ለስፖርቱ ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት ለሌሎች ሀገራት ልምድና ተሞክሮ የሚሆን ነው ማለታቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

በዓለም አደባባይ ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ ያደረጉ ብርቅየ አትሌቶች መገኛዋ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ታሪክን በመዘከር እና አዳዲስ ታሪኮችን በመፃፍ ላይ ትገኛለች፡፡

አዲስ አበባ ከተማ የስፖርት ቱሪዝም ማዕከል ለመሆን በሰራችዉ ስራ እና ባስመገበችዉ ድል የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የአንድ ቀን ሩጫ የአዲስ አበባ ግራን ፕሪ ውድድርን በስኬት ማስተናገዷ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.