Fana: At a Speed of Life!

የአለም ኢኮኖሚ ክፉኛ እየባሰ እንደሚመጣ የዓለም ምጣኔ ሀብት (IMF) ትንበያ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)ዓለም አሁን ካለው የኢኮኖሚ ችግር በባሰ ሁኔታ እንደሚቀጥል የዓለም ምጣኔ ሃብት ግምቱን አስታውቋል፡፡

ዓለም አቀፉ የዓለም ምጣኔ ሃብት ተቋም በዚህ ዓመት የአለም ኢኮኖሚ 4ነጥብ 9 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅሶ በዚህም ድርጅቱ የኮሮና ቫይረስ ካስከተለው ችግር ለመውጣት እየታገለ መሆኑን አሰታውቋል፡፡

አነስተኛ እና ትላልቅ የንግድ ድርጅቶችና ኢኮኖሚያቸው በዚህ ወቅት ክፉኛ እየተጎዱ መሆናቸውን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ የሚያደርገው ድጋፍም እንዲሁ በቀጣዩ ዓመት ሊቀንስ እንደሚችል ነው ግምቱን ያስቀመጠው ፡፡

አሁን ከሚመጣው ሚያዝያ ትንበያ ጋር ሲነፃፀር በሚቀጥለው አመት የአለም ዕድገት በ5ነጥብ4 ዝቅ ሊል ይችላል ነው የተባለው፡፡

ኢኮኖሚስቶች ድንበሮች ሲዘጉ ፣ የንግድ ተቋማት መዘጋት እና የአለም አቀፍ ምጣኔ ሀብት ዘርፎች በሙሉ መዘግየት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የሚደረጉ እርምጃወችን በአግባቡ በመተግበር ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቀውን የኢኮኖሚ ውድቀት ለመቋቋም እየተሞከረ ነው ብለዋል፡፡

ድርጅቱ ባወጣው የቅርብ ጊዜ የአለም ኢኪኖሚ ሁናቴን የሚያሳይ እትም ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ለረጅም ጊዜ የእንቅስቃሴ እግድ መጣል ኢኮኖሚው ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ላይ ጥንቃቄ እንዲወሰድ አስጠንቅቀዋል፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.