በተወረወሩብን የዕንቅፋት ድንጋዮች ኢትዮጵያን ገንብተንበታል – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተወረወሩብን የዕንቅፋት ድንጋዮች ኢትዮጵያን ገንብተንበታል ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ዐቅሟ ትልቅ፤ ጸጋዋ ብዙ፤ ዕድሏ ሰፊ፤ መሆኑን ዐውቀናል ብለዋል።
የኢትዮጵያ የማንሠራራት ዘመን ነው በማለት ገልጸው፤ ትውልድ ሲጠይቀው የኖረውን የኢትዮጵያ ብልጽግና እውን እናደርገዋለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።