የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር መልዕክት
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ለተመረጡት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለምክትል ፕሬዚዳንቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
በመልዕክታቸውም÷ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ለተመረጡት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ምክትል ፕሬዚዳንት ለሆኑት አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አደም ፋራህ መልካም የሥራ ጊዜን ተመኝተዋል፡፡