አቶ አረጋ ከበደ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።
በዚህ መሠረት ዶ/ር እሸቱ የሱፍ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ፣ ኮሚሸነር ዘላለም መንግስቴ የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም አቶ አስቻለ አላምሬ የሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን የአማራ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡