በአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጫናን ለመቋቋም የምግብ ስርዓትን ማዘመን ይገባል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጫናን ለመቋቋም የተፈጥሮ ሃብትን በተገቢው ጥቅም ላይ በማዋል የምግብ ስርዓትን ማዘመን ይገባል።
ኢትዮጵያ ከጣሊያን እና ከተባበሩት መንግስታት ጋር በመተባበር ያዘጋጀችው ሁለተኛው የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ እንዳሉት፤ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ዓለም አቀፍ የምግብ ስርዓት መጓደልና ሌሎች በርካታ ተግዳሮቶች ሀገራትን እየፈተኑ ይገኛል።
ሀገራት የፖለቲካ ቁርጠኝነትን በመላበስ የሚባክነውን ምግብ ለተቸገሩ ወገኖች ተደራሽ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ዓለም አቀፉን የምግብ ስርዓት የማይበገርና ተደራሽ በማድረግ ረሃብን ዜሮ ለማድረስ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት በቁርጠኝነት መስራት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
አፍሪካ ያልተነካ እምቅ የተፈጥሮ ሃብትና ያልታረሰ መሬት ያላት በመሆኑ ጥቅም ላይ ያልዋሉ ሀብቶችን አገልግሎት እንዲሰጡ መስራት እንደሚገባም ነው የጠቆሙት፡፡
አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ እየተፈነች በመሆኗ እነዚህን ችግሮች ለመከላከል የምግብ ስርዓታችንን ማዘመን አለብን ብለዋል፡፡
የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ በበኩላቸው እንዳሉት፤ አካታች የኢኮኖሚ እድገት ለዘላቂ የምግብ ሥርዓት መረጋገጥ አይነተኛ ሚና አለው፡፡
የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ በዜጎች ላይ ትርጉም ያለውን ለውጥ ለማምጣት አይነተኛ ሚና ያለው ዓለም አቀፋዊ እሳቤ መሆኑን ጠቅሰው፤ የምግብ ስርዓትን ለማረጋገጥ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ወሳኝ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
ለዚህም በስራ ዕድል፣ በኢንቨስትመንትና በአቅም ግንባታ ተግባራት ላይ የጋራ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉም ገልጸዋል።
የምግብ ሥርዓትን ለማስጠበቅ የሚደረጉ ስምምነቶች የታለመላቸውን ግብ እንዲመቱ የአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማጠናከር እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!