Fana: At a Speed of Life!

በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአካል አጀንዳ የማሰባሰቡ ሥራ ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በውጭ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአካል አጀንጃ የማሰባሰብ ሥራውን በነገው ዕለት ይጀምራል፡፡

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጥበቡ ታደሰ በሰጡት መግለጫ÷ የምክክር ኮሚሽኑ በውጭ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በበይነ መረብ አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

በነገው ዕለትም በአካል የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ አምስት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች በተገኙበት እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ በሰሜን አሜሪካ፣ ስዊድን እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አጀንዳ ለማሰባሰብ ዝግጅት መደረጉን ነው ያስረዱት፡፡

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለዚህ ዓለማ በተዘጋጀው የበይነ መረብ አማራጭ እንዲመዘገቡም አቶ ጥበብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በክብረወሰን ኑሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.