Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከ21 ሺህ በላይ መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና እየወሰዱ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል 21 ሺህ 323 የትምህርት ቤት አመራሮች እና መምህራን ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የክረምት ልዩ አቅም ግንባታ ስልጠና እየወሰዱ ነው አለ የክልሉ ትምህርት ቢሮ።

በምክትል የቢሮ ኃላፊ ደረጃ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ኤፍሬም ተሰማ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ስልጠናው መምህራን በሚያስተምሯቸው የትምህርት ይዘትና በማስተማር ስነ ዘዴ ላይ ያተኮረ ነው።

መምህራን እና የትምህርት አመራሮች የመማር ማስተማር ስራቸውን የሚያስችለው ስልጠና በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል።

ስልጠናው መምህራን ብቁ ሆነው ዕውቀታቸውን ለተማሪዎቻቸው ማስተላለፍ የሚችሉበትን ዕድል ያሰፋል ነው ያሉት።

የትምህርት አመራሮች በመማር ማስተማር ስራ ላይ በማተኮር መምራት የሚችሉበትን አሰራር በተመለከተ የተዘጋጁ ሞጁሎችና ሌሎች ማኑዋሎች ላይ ግንዛቤ እንዲጨብጡ እንደሚደረግም አንስተዋል።

በየጊዜው ለመምህራንና ትምህርት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚሰጥ አስታውሰው÷ በክልሉ የምርምርና ስልጠና ማዕከል በ2017 ዓ.ም ከ30 ሺህ በላይ መምህራን፣ የትምህርት ባለሙያና አመራሮች ስልጠና ሲወስዱ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ከ3ኛ እስከ 5ኛ ክፍል ላሉ ለ54 ሺህ የአፋን ኦሮሞና ሒሳብ መምህራን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ከነሐሴ 3 ጀምሮ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።

ሥልጠናውም በክልሉ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን የማንበብ፣ መፃፍና የማስላት ችግሮችን ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

በተመሳሳይ ለ4 ሺህ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህራን በተያዘው ክረምት ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን አመልክተዋል።

በአጠቃላይ ስልጠናዎቹ በትምህርት ጥራት ላይ በጥናት የተለዩትን ችግሮች ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አላቸው ነው ያሉት።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.