Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገነቡ 1ሺህ 671 ቤቶች ለህብረተሰቡ አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገነቡ 1 ሺህ 671 ቤቶችን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስረክበዋል።
የተገነቡት ቤቶች ለሀገር ባለውለታዎች፣ ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለከፋ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ እንዲሁም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙና በወንዝ ዳርቻዎች ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሰጥተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳሉት፥ ቤቶቹ የህፃናት መጫወቻዎችንና የስፓርት ማዘውተሪዎችን የያዙ ሲሆን፥ አብሮነትንና ጉርብትናን የሚያጠናክሩ ንፁህና የሰው ልጅ የሚገባውን የከበረ የአኗኗር ዘይቤ የሚያዳብሩ ናቸው፡፡
በክረምት የበጎ ፍቃድ ተግባር 2500 ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ እንደነበር አስታውሰው፥ ከ3 ሺህ በላይ ቤቶችን በመገንባት ከእቅድ በላይ መፈፀም ተችሏል ነው ያሉት።
በዚህም በዛሬው ዕለት ለለህብረተሰቡ ከተላለፉት ቤቶች በተጨማሪ ቀሪዎቹ በዚህ ወር መጨረሻ ተጠናቅቀው ርክክብ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።
ከንቲባዋ ይህን በጎ ተግባር በእውቀታቸው፣ በሀብታቸውና በጉልበታቸው ለደገፉ ባለሀብቶች እና ላስተባበሩ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በአንዷለም ተስፋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.