Fana: At a Speed of Life!

የሀገራችንን ህልውናና ብሔራዊ ጥቅሞች ለመጠበቅ ሠራዊቱ ከምንግዜውም በላይ ዝግጁ ነው – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገራችንን ህልውናና ብሔራዊ ጥቅሞች ለመጠበቅና ለማስከበር ሠራዊቱ ከምንግዜውም በላይ ዝግጁ ነው አሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፡፡
የሁርሶ አጭር ኮርስ እጩ መኮንን ትምህርት ቤት የ26ኛ ንስር ኮርስ ሰልጣኞችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ለተመራቂ መኮንኖች ባስተላለፉት መልዕክት፥ የቀደምት አርበኞች ልጆች በመሆናችሁ ሀገርን ጠብቃችሁ ለትውልድ ማስረከብ ይጠበቅባችኋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ በንግግራቸው፥ ሠራዊታችን የትኛውንም ተልዕኮ በብቃትና በቁርጠኝነት መወጣት የሚያስችለውን የዘመኑን ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ቀስሟል ነው ያሉት።
ተመራቂዎች በስልጠናው በቀሰማችሁት የንድፍና የተግባር ልምድና እውቀት ከፍ ብላችሁ እንደ ንስር በመብረር ለሀገር ከፍታና ሉዓላዊነት መስራት ይኖርባችኋል ብለዋል።
ሀገራችን የተፈጥሮ ሀብቷን እንዳትጠቀም የሚፈልጉ ጠላቶቿ ባንዳዎችን በመመልመልና የውስጥ ቀዳዳን በመፍጠር ሀገርን ለማተራመስ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ይህን ታላቅ ህዝብና ሀገር የሚመጥን ዘመናዊ ሰራዊት ገንብተን የሀገርን ብሔራዊ ጥቅሞች በአስተማማኝ መንገድ የመጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነታችንን እየተወጣን እንገኛለን ነው ያሉት።
በዚሁ የዕጩ መኮንኖች የምረቃ ስነስርዓት ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላን ጨምሮ ጀኔራል መኮንኖች እና የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሀር ተገኝተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.