ቶተንሀም ሊድስ ዩናይትድን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቶተንሀም ሆትስፐር ሊድስ ዩናይትድን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
ቀን ከ8:30 ላይ በሊድስ ሜዳ ኢላንድ ሮድ በተካሄደው ጨዋታ ቶተንሃም ድል ቀንቶታል።
በዚህም ፈረንሳዊው ማቲይስ ቴል እና ጋናዊው ሞሀመድ ኩዱስ የቶተንሀምን ግቦች አስቆጥረዋል።
ሊድስ ዩናይትድ ከሽንፈት ያልታደገውን ብቸኛ ግብ ስዊዘርላንዳዊው የክንፍ አጥቂ ኖህ አካፎር ከመረብ አሳርፏል።