በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ቼልሲ ሊቨርፑልን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ተጠባቂ ጨዋታ ቼልሲ ሊቨርፑልን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
ምሽት 1፡30 ላይ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ሊቨርፑልን ያስተናገደው ቼልሲ ካሴዶ እና ኢስቲቫኦ ባስቆጠሯቸው ግቦች ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
የሊቨርፑልን ብቸኛ ግብ ጋክፖ አስቆጥሯል።
ቀን 11 ሰዓት ላይ በተካሄዱ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ሰንደርላንድን እንዲሁም አርሰናል ዌስትሀምን 2 ለ 0 በሆነ ተመሳሳይ ውጤት ማሸነፋቸው ይታወቃል።