ቅዱስ ጊዮርጊስ ባህርዳር ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ባህርዳር ከተማን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ቀን 7:00 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ አቤል ያለው (ሁለት) እና አዲሱ አቶላ ባስቆጠሯቸው ግቦች ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
ባህር ዳር ከተማ ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ በረከት ጥጋቡ አስቆጥሯል።