Fana: At a Speed of Life!

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ፣ ሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ፣ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሁለቱ ወገኖች በቀጣናዊና አህጉራዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ የመከሩ ሲሆን፥ የሰላምና ጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ትብብራቸውን ማጠናከር እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በያዝነው የፈረንጆቹ ወር የኅብረቱ የፖለቲካ፣ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ምክር ቤት ሊቀመንበር መሆኗ ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.