በኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ጌታቸውና አትሌት መሰለች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ በተካሄደው 19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በወንዶች አትሌት ጌታቸው ማስረሻ ከሸገር ሲቲ እንዲሁም በሴቶች አትሌት መሰለች አለማየሁ ከአዲስ አበባ ፖሊስ አሸንፈዋል፡፡
በወንዶች ምድብ አትሌት ባለይልኝ ተሻገር ከኢትዮ ኤሌክትሪክ 2ኛ ሲወጣ አትሌት በላይ ጥላሁን ደግሞ ከአዲስ አበባ ፖሊስ 3ኛ ደረጃን ይዟል፡፡
ውድድሩ በዴንማርክ ኮፐንሀገን ለሚካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችን ለመምረጥና ተተኪዎንች ለማፍራት ያለመ ነው፡፡