Fana: At a Speed of Life!

የአባቱን ፈለግ የተከተለው የዲያጎ ሲሞኔ ልጅ ጁሊያኖ ሲሞኒ…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአትሌቲኮ ማድሪዱ ስኬታማ አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኔ በተጫዋችነት ዘመኑ ለሀገሩ አርጀንቲና ትልቅ ክብርና ስኬትን ካስመዘገቡ ታላላቅ ኮከቦች ተርታ ይመደባል።

ለሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ከ100 በላይ ጨዋታዎችን ያደረገው ሲሞኔ÷ አልቢሴሌስቴዎቹ በ1991 እና 1993 የኮፓ አሜሪካ ዋንጫን ሲያነሱ የቡድኑ የልብ ትርታና የሜዳ ላይ መሪ በመሆን ታሪክ ሰርቷል።

አሁን ደግሞ የዚህ ታላቅ ተጫዋች ፈለግ በልጆቹ እየተደገመ ይገኛል።

የአባቱን ፈለግ የተከተለው ወጣቱ ጁሊያኖ ሲሞኔ ከቀናት በኋላ በሚጀምረው የ2026 ዓለም ዋንጫ ላይ የአርጀንቲናን ብሔራዊ ቡድን ወክሎ ለመጫወት ተዘጋጅቷል።

በአሁኑ ሰዓት በአትሌቲኮ ማድሪድ ቤት በአባቱ ስር እየተጫወተ የሚገኘው ጁሊያኖ÷ ቀደም ሲል በአርጀንቲና ከ23 ዓመት በታች የኦሊምፒክ ቡድን ውስጥ በመካተት ሀገሩን መወከል ችሏል።

ይህ የቤተሰብ ስኬት በጁሊያኖ ብቻ የተገደበ ሳይሆን ከዚህ በፊት የዲያጎ ሲሞኔ የመጀመሪያ ልጅ የሆነው ጆቫኒ ሲሞኔም በተመሳሳይ ለዋናው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በመጫወት ግብ ማስቆጠር መቻሉ ይታወሳል።

አባት በክብር የተጫወተባትን ማልያ ልጆቹም ደግመው በመልበስ የቤተሰቡን ስም በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ላይ በደማቅ ቀለም እየጻፉት ይገኛሉ።

በሙባረክ ፋንታው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.