Fana: At a Speed of Life!

ጎንደር የሚገባትን ያጣች፤ ገና ብዙ ሊሰራላት የሚገባ ከተማ ናት – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጎንደር የሚገባትን ያጣች፤ ገና ብዙ ሊሰራላት የሚገባ ከተማ ናት አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የመገጭ ግድብ ፕሮጀክትን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ ፕሮጀክቶችን ከጀመሩ በኋላ በተገቢው ጊዜ ማጠናቀቅና ለሕዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡
ቃል ከገቡ በኋላ ፕሮጀክቶችን ማዘግየት ግን የከፋ ጥፋት መሆኑን አስገንዝበዋል።
ከሁለት ዓመት በፊት ፕሮጀክቱን በቦታው ተገኝተው መመልከታቸውን አስታውሰው፤ ፕሮጀክቱ በባለቤትነት የተያዘ እንደማይመስል እና ለ19 ዓመታት ያህል ከፍተኛ ሀብት እየባከነ ሕዝቡ በውሃ ጥም ሲቸገር መቆየቱን ገልጸዋል።
ይህንን የተጓተተ አሰራር “እርግማን” በመባል ሲጠራ እንደነበር ጠቁመው፤ ያንን እርግማን ነቅሎ ወደ በረከት ለመቀየር የተከናወነው ተግባር የፋይናንስ በጀት መመደብ ብቻ ሳይሆን፤ ኮንትራክተሩን የመቀየር ርምጃ ጭምር መሆኑን አብራርተዋል።
ቀድሞ ተሰርቶ የነበረውና ለጎንደር ከተማም ሆነ ለግድብነት የማይመጥነውን ሥራ በማፍረስ ላለፉት ሁለት ዓመታት ገደማ በባለቤትነት ስሜት በተሰራው ጥረት ፕሮጀክቱ ለፍሬ ሊበቃ መቻሉን አመልክተዋል።
በመልካም ፈቃዱ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.