የጎንደርን እንዲሁም የመላው አማራ ክልልን ልማት ለማፋጠን ቀን ከሌት እንተጋለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎንደርን እንዲሁም የመላው አማራ ክልልን ልማት ለማፋጠን ቀን ከሌት እንተጋለን አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት የመገጭ ግድብ ፕሮጀክትን መርቀው አገልግሎት ባስጀመሩበት ወቅት ነው።
በጎንደር በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በኩል በተከናወኑ የልማት ተግባራት እንዲሁም በመገጭ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የተሰማቸውን ደስታ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጎንደርን እንዲሁም የመላው አማራ ክልልን ልማት ለማፋጠን ቀን ከሌት እንተጋለን ብለዋል።
የኢትዮጵያን ሥልጣኔ ለመፍጠር መንግሥት እየተጋ ይገኛል፤ የእኛ ሥራ ሀገር መገንባት እንጂ ከምርጫ ጋር ትስስር የለውም፤ ቃል የገባነውንም እንፈጽማለን ሲሉ ተናግረዋል።
ታሪክና ባሕላችንን ለተቀረው ሕዝብ በአግባቡ ማሳየት እንድንችል፣ እንዲሁም ጎንደር ደርሶ መመለሻ ብቻ ሳትሆን መቆያም እንድትሆን የሚያስችሉ ማረፊያዎች ሊገነቡ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ዕድገትና ሥልጣኔ አፍሪካ ውስጥ እንዳለ ማወቅ ለምትፈልጉ ሰዎች ፋሲል አለላችሁ፤ ስቆ የሚቀበላችሁ ሕዝብ ዘንድ እየመጣችሁ የአፍሪካን ሥልጣኔ ማወቅና መማር ጠቃሚ ነው ብለዋል።
የሚሠሩ ዘላቂ የልማት ሥራዎች ከወቅቱ የሥራ ኃላፊዎች ይልቅ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ በመሆናቸው መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በክልሉ ልማት ላይ ለተሳተፉ ባለድርሻ አካላት ምስጋና ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በቀጣይ በሚከናወኑት የልማት ሥራዎች ላይም አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ አደራ ብለዋል።
በምሕረት ደምሴ