Fana: At a Speed of Life!

የተቋማት ሪፎርምና ብቁ አመራር ለኢትዮጵያ የከፍታ ጉዞ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመደመር መንግሥት ሀገራዊ ለውጡን ወደ ላቀ ምዕራፍ እንዲያደርሱ ትኩረት ካደረገባቸው ጉዳዮች ውስጥ የተቋማት ሪፎርም ዋነኛው ነው።

በዚህ ረገድ በተቋማት ዘመናዊ አሠራርን መገንባት፣ ቢሮክራሲን ማስወገድ፣ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነትን ማስፈን ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው።

ተቋማዊ ለውጥ ብቻውን በቂ አይደለም፤ ተቋማቱን የሚመሩና የውሳኔ ሰጪነት ሚና ያላቸውን ኃላፊዎችን አቅም አብሮ ማሳደግ መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡

ለዚህም መንግሥት በሀገሪቱ የተለያዩ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ አመራሮችን የአመለካከትና አቅም ግንባታ ሥልጠናዎች እየሰጠ ነው፡፡ ብቁና ታታሪ አመራር መፍጠር ተቋማት ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ተጠያቂነት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ ያስችላቸዋል፡፡

ተቋማትን ብቻ ሳይሆን የተቋማት መሪዎችን ማብቃት በከፍታ ለምትጓዝ ሀገር ወሳኝነት አለው፤ የአመራርነት ቦታ ላይ ለሚገኙ ኃላፊዎች ዕውቀትን፣ የአገልጋይነት መንፈስን እና ሥነ ምግባርን አጣምረው የያዙ እንዲሆኑ እየተሰራ ይገኛል።

ሥልጠናዎች ለአመራሮች የአመለካከት ለውጥ እንዲኖር፣ የሀገርን እና የዓለምን ሁለንተናዊ ነባራዊ ሁኔታዎች በጥልቀት እንዲረዱ እና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በጋራ እንዲያመነጩ ሰፊ ዕድል የሚፈጠር ነው።

በዚህም የቢሮክራሲ አሠራርን በማስቀረት፣ ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ተዓማኒነት ያላቸው ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ህዝብን በቅንነትና በታታሪነት እንዲያገለግሉ እያገዘ ነው፡፡

ይህም በየደረጃው የሚገኙ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታየውን መሻሻል በቀጥታ እያገዘው ይገኛል። አመራሮችን ማብቃት የውሳኔ አሰጣጥ ሂደትን ፈጣንና ፍትሃዊ እንዲሆን፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ያደርጋል።

ብቃት ያለው አመራር ችግሮችን ከጅምራቸው በማየት መፍትሔዎችን እንዲያመነጭ፣ ሙስናንና ብልሹ አሠራሮችን በመዋጋት ረገድ ቁርጠኛ አቋም እንዲይዝ የሚያስችል ሲሆን በህዝብ ዘንድ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመቀነስ የመንግሥትን ተቋማት ተዓማኒነት ከፍ ያደርጋል።

ከዚህም ባሻገር በየደረጃው ያለው አመራር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና ዘመናዊ የአስተዳደር ዘዴዎችን የመቀበል አቅሙ እንዲዳብር አድርጓል።

ዓለም በየሰዓቱ የምትቀየርበትን ፍጥነት የሚመጥን ብቁ የሰው ኃይል መፍጠር፣ የሀገሪቱ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ዕድገት አስተማማኝ መሠረት እንዲይዝ ያደርጋል።

የመደመር መንግሥት አመራሮች በፍጥነት ለሚለዋወጠው የዓለም ስርዓት በሚመጥን መልኩ እንዲዘጋጁ እየሰራ ይገኛል።

በሌላ በኩል የአመራር አቅም ግንባታ በመንግሥትና በህዝብ መካከል ያለውን መተማመን ያጠናክራል፡፡ ዜጎች የሚመሩዋቸው አካላት ብቁና በሥነ ምግባር የታነጹ መሆናቸውን ሲገነዘቡ የመንግሥት ሥራዎችን የመደገፍና በባለቤትነት የመሳተፍ ፍላጎታቸው ይጨምራል።

በመሆኑም የመደመር መንግሥት የተቋማት ሪፎርም ከቴክኒክ እና ከአሠራር ማሻሻያ ባሻገር የሰው ኃይልን በማብቃት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ይህ አመራርን የማብቃት ሂደት ለቀጣዮቹ የልማትና የሰላም ምዕራፎች ጠንካራ መሠረት ለመጣል ያስችላል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

በቤተልሔም ግርማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.