Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
መስተዳድር ምክር ቤቱ በዋናነትም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ከ2 ነጥብ 65 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 16 አልሚዎች የመስሪያ ቦታ በምደባ እንዲሰጥ ውሳኔ አስተላልፏል።
የመስሪያ ቦታ እንዲሰጥ ውሳኔ የተላለፈውም በልዩ ሀገራዊና ክልላዊ ፋይዳ ባላቸው በተለይ በሆቴልና ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪና ማኑፋክቸሪንግ፣ የእርሻና ምርት ማቀነባበሪያ፣ በቅይጥ አገልግሎትና በሆስፒታል እንዲሁም ለመዝናኛ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች ነው።
የመሬት ምደባ የተደረገላቸው ባለሀብቶች በሚሰማሩበት የልማት መስክም ሀገራዊና ክልላዊ ፋይዳ ያላቸውና ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስለመሆናቸው ተጠቁሟል።
ለባለሃብቶቹ የተሰጠው መሬት ለተፈለገው ልማት እንዲውልና በአፋጣኝ ወደ ስራ እንዲገቡ አቅጣጫ የተሰጠ ሲሆን፤ የክልሉ መንግስት የኢንቨስትመንት ዘርፉን የበለጠ ለማነቃቃት በትኩረት እየሰራ መሆኑም ተመላክቷል።
መስተዳድር ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.