የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ቱርክዬ አንታሊያ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ-32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በኮፕ-31 ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ቱርክዬ አንታሊያ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከኮፕ-31 ፕሬዚዳንት፣ ከተለያዩ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተደራዳሪ ቡድኖችና ከአጋር አካላት ጋር ይወያያሉ፡፡
ውይይቶቹ ከኮፕ-31 ወደ ኮፕ-32 የሚደረገውን ሽግግር በተሳለጠ ሁኔታ ለማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡
በተጨማሪም በአዲስ አበባ የሚካሄደው ኮፕ-32 አካታች፣ በተግባር ላይ ያተኮረና ተጨባጭ ውጤት የሚያስገኝ እንዲሆን የጋራ መግባባትንና ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ነው።