Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ90 ሺህ አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ90 ሺህ አልፏል።

ባለፉት 24 ሰዓታትም ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 602 የላብራቶሪ ምርመራ 630 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 90 ሺህ 490 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ባለፈ የ6 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 371 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 489 ሰዎች ከኮሮና ቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 43 ሺህ 638 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 410 ሺህ 496 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 90 ሺህ 490 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 45 ሺህ 104 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 237 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 45 ሺህ 479 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ1 ሺህ 371 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.