Fana: At a Speed of Life!

ለመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ከ34 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ ከ34 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን የከተማው አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የአስተዳደሩ የሎጅስቲክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አደባባይ ሙሉጌታ እንደገለጹት ÷ ድጋፉን ያደረጉት በ35 የሴክተርና በ66 በክፍለ ከተማ ተቋማት የሚሰሩ ሠራተኞች ናቸው፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሀገር ደህንነትና በክልሉ ሕዝብ ላይ የደቀነውን ስጋት ለመመከት ሕዝባዊ ድጋፍ የሚያስተባብር አንድ አቢይና ሶስት ንኡሳን ኮሚቴዎች ተዋቅረው ወደ ሥራ መገባታቸውን ገልጸዋል፡፡
ከከተማው ነዋሪዎች ከአጎራባች የገጠር ቀበሌዎች 169 ሚሊየን ብር በማሰባሰብ ወደ ግንባር ለዘመተው ኃይል ድጋፍ ለማሰባሰብ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
እቅዱን ለማሳካትም ከመንግሥት ሠራተኞች፣ ከከተማው ነዋሪዎች፣ ከባለሃብቶች፣ ከንግዱ ማህብረሰብ ፣በውጭ ከሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች እንዲሁም ከፋይናንስ ተቋማት ድጋፍ ለማሰባሰብ መታቀዱን ገልጸዋል።
የመንግስት ሰራተኞቹ የአንድ ወር ደመወዛቸውን መስጠታቸውን የገለጹት አቶ አደባባይ÷ የከተማውን ማህብረሰብ በማወያየት ሀገርን ለማዳን ሕዝባዊ ደጀንነቱን ለማጠናከር እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.