የአፋር ሱልጣኔት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ብልጽግና ፓርቲ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማሸነፋቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባለፉት የለውጥ ዓመታት ትልቅ እመርታ ያስመዘገቡ ኢኮኖሚዊና ፖለቲካዊ የሪፎርም ሥራዎች ማከናወናቸውን አስታውሰዋል፡፡
እነዚህ የለውጥ ርምጃዎች የኢትዮጵያን ሁንተናዊ ልማትና ብልጽግና እንዲሁም ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከር ያለሙ መሆናቸውን አውስተዋል፡፡
ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ የኢትዮጵያ ሕዝብ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚበጀውን ፓርቲ ለመምረጥ ያሳየውን ጠንካራ እና ንቁ ተሳትፎ በማድነቅ አመስግነዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የጀመሩትን ሁለንተናዊ የለውጥ ሒደት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እምነታቸው መሆኑን ገልጸው÷ የአፋር ሱልጣኔት የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ለማድረግ በትብብር እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡