ብሔራዊ የዲጅታል ክፍያ ስትራቴጂ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ የዲጅታል ክፍያ ስትራቴጂ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የብሔራዊ ባንክ አመራር አባላት የተባበሩት መንግስታት የልማት የካፒታል ፈንድና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
የብሔራዊ ባንክ የክፍያ ስርዓትና ሴትልመንት ዳይሬክተር ወይዘሮ ማርታ ሀይለማርያም እንዳሉት የዲጅታል ክፍያ አገልግሎት ከግለሰብ ጀምሮ እስከ መንግስት ባሉ የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ የሚጫወተው ሚና ጉልህ ነው።
የዲጅታል ክፍያ አገልግሎት በኢትዮጵያ በጅምር ላይ መሆኑን ጠቅሰው ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ክፍያን በቀላል፣ በአነስተኛ ወጪ እና ጊዜ አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለመፈፀም ይረዳል ነው ያሉት።
የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን እርካታ መጨመር እና የዘርፉን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለሃገራዊ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!