Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የሞባይል መመርመሪያ መሳሪያ ግዢ ፈጸመ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የዲጂታል ፎረንሲክ ምርመራ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የሞባይል መመርመሪያ መሳሪያ (celebrate Machine) ግዢ ፈጸመ፡፡

ከእስራኤል ለተገዛው መሳሪያ 110 ሺህ 600 ዶላር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ወደስራ ለማስገባት ለሙያተኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግስቴ የስራ ዘርፉን ይበልጥ ለማደራጀት በርካታ ገንዘብ ወጪ ተደርጎበት የተገዛ በመሆኑ ባለሙያዎቹ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲያዉሉ አሳስበዋል፡፡

የበይነ መረብ ወንጀሎች ምርመራ ዲቪዥን ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ዳኜ ነጋሽ በበኩላቸው፥ መሳሪያው ዘመናዊነትን የተላበሰና አሁን ዓለም በዘመናዊ መንገድ የሚጠቀመው በመሆኑ ማናኛውንም ሞባይል መመርመር የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም የወንጀል ምርመራ ቢሮው የዲጂታል ፎረንሲክ ምርመራን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ የተለያዩ ዘመናዊ የሆኑ የመመርመሪያ መሳሪያዎችን ወደስራ ለማስገባት እየሰራ ነው ማለታቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.