Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ቡድን  በራያ ቆቦ  አስከፊ ጭፍጨፋ  መፈጸሙን  የዓይን እማኞች ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን  ጳጉሜን 4  ቀን 2013 በራያ  ቆቦ በፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ አርሶ አደሮችን፤  ህፃናትንና እናቶችን  ጭምር ከቤት እያወጣ መረሸኑን ከጭፍጨፍው አምልጠው የወጡ የዓይን እማኞች ተናገሩ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት  ሪፖርተሮች ጋር ቆይታ ያደረጉና የአሸባሪውን ቡድን ጭፍጨፋ የተመለከቱ የዓይን ምስክሮች በራያ ቆቦ በርካቶች ያለ ርህራሄ  በጅምላ ተገድለዋል ብለዋል።

በአከባቢው ነዋሪ የነበሩት አቶ ካሳው አማረ ወራሪ  ቡድኑ በቦታው ከገባ በኋላ ሴቶችን መድፈርና ህጻናትን መግደል የዘወትር ተግባሩ መሆኑን ገልጸው፥  “አርሼ በበላሁ ልጆቼን ሳላሳድግ ቀኝ እጄን በጭካኔ ቆረጠው” ብለዋል።  ጳጉሜን 4  አረመኔው ቡድን ባካሄደው ጭፍጨፋ ከ50 በላይ አስክሬን መመልከታቸውንም ተናግረዋል።

ይህ አሸባሪ ቡድን ለፍቶ አዳሪ አርሶ አደሮችን እርሻቸው ላይ በግፍ ገድሏቸዋል ብለዋል።

እጄ ተቆርጦ 7 ቀን ሙሉ ደም  ሲፈሰኝ ነበር  ያሉት አቶ ካሳው፥  5 ልጆቻቸውና ባለቤታቸው በቦታው የሚገጥማቸው እጣ ፈንታ ዛሬም እንደሚያሳስባቸው ነው የሚናገሩት።

ሌላኛው የዓይን እማኝ አቶ በላይ እያሱ እንደተናገሩት  ጁንታው ጳጉሜን 4 ቆቦ ላይ ስራ ፍለጋ የመጡ 16 የቀን ሰራተኞችን በመግደል የማይካድራውን ዓይነት ጭፍጨፋ ፈጽሟል።

ህጻናትን ወደ ገደል ጥሏል፥  በርካታ ሴቶችና ወጣቶችን ያልታወቀ ቦታ በመውሰድ ሰውሯቸዋል።

በስናይፐር  ጥይት ፌታቸውን ተመትተው ከሞት የተረፉት አቶ መንገሻ አሊ በበኩላቸው  በየቀኑ የጁንታው ቡድን አባላት ቤት ለቤት እየዞሩ የበርካታ ንጹሃንን ህይወት አጥፍተዋል ነው ያሉት።  የቅርብ ጎደኞቻቸውን ጨምሮ 15 አሰክሬን መመልከታቸውንም ነግረውናል።

በአንድ ቀን ብቻ በድኑ በራያ ቆቦ  ነዋሪዎች ላይ ባደረስው ጭፍጨፋ በርካታ ንጹሃን ዜጎች መመታቻውን የተናገሩት የዓይን እማኞቹ፥  በዞብል በኩል አምልጠው በመምጣት  ህይወታቸውን ለማትረፍ መቻላቸውን ገልጸዋል። ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ   በርካታ  የአካባቢው   ንጹሀን  ዜጎች  ከፍተኛ ጭንቀትና ስጋት ላይ መሆናቸውን  ነው በአጽንኦት የተናገሩት ።

በደሴ ሆስፒታል በህክምና ክትትል ላይ የሚገኙትና ከጳጉሜን 4ቱ የራያ ቆቦ ጭፍጨፋ የተረፋት የዓይን እማኞች ከሰው አልፎ ስንጠቀምባቸው የነበሩ  የጋሪ ፈረሶች  የገደለው ጁንታ፥  ሌላ  የከፋ ጥፍት ሳያደርስ የሚመለከታቸው አካላት ሊደርሱልን  ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።

በራያ ቆቦ ቤተሰብ ያለው ወጣት በሙሉ እራሱን አዘገጅቶና ሰራዊቱን ተቀላቅሎ ወደ ግንባር በመግባት ይሄ አረመኔ ቡድን ተጠራርጎ ካልጠፋ የህሊና እረፍት ልናገኝ አንችልም ብለዋል።

በከድር መሀመድ እና በሀብታሙ ተክለስላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.