Fana: At a Speed of Life!

የግሸን ደብረ ከርቤ አመታዊ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የዘንድሮው የግሸን ደብረ ከርቤ አመታዊ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር መጠናቀቁን የደቡብ ወሎ ዞን ፓሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
 
የመምሪያው ሀላፊ ኮማንደር እርገጤ ጌታሁን ÷በዓሉ ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁንና ምዕመናን ወደየመጡበት ቦታ እየተመለሱ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
 
በበዓሉ ወቅት በተደረገ ጥብቅ ቁጥጥርም 48 ጸጉረ ልውጦች መያዛቸውን የተናገሩት ሀላፊው ÷35ቱ በተደረገ ማጣራት ሲለቀቁ 13ቱ በህግ ስር ሆነው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ።
 
በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ከፍተኛ ሚና መወጣታቸውን ኃላፊው ገልፀው ጥቃቅን ወንጀሎች እንዳይፈጸሙ በማደረግ በኩልም የተሻለ ስራ ሰርተዋል ብለዋል።
 
የጸጥታ አካላት በቅንጅት መስራታቸውም በዓሉ በሰላም ለመከበሩ ትልቁ ተግባር ነበር ነው ያሉት፡፡
 
ሀላፊው ቀጣይ በዓላትንም በጋራ በመስራት ሰላማቸው የተጠበቀ ማድረግ ይገባል ያሉ ሲሆን÷ የዞኑ ፓሊስ መምሪያ ሀላፊነታቸውን በትጋት ለተወጡ ሁሉ ምስጋና ያቀርባል ብለዋል።
 
በከድር መሀመድ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.