Fana: At a Speed of Life!

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል በይፋ መቋቋሙ ተገለፀ፡፡

ማዕከሉ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመ ሲሆን ÷በመድረኩ የዓባይ ውሃና የተፋሰሱ ሀገራትን ፍላጎት እንዲሁም አሁናዊ የሀገሪቷ ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን በሚመለከት ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖም ÷ግብፅ በአባይ ላይ ያላት ፅኑ ፍላጎትና በተፋሰሱ ሀገራት መካከል ሲደረጉ የነበሩ የድርድር ሂደቶች ምን መልክ እንደነበራቸው ገለፃ አድርገዋል።

የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ በበኩላቸው÷ ተቋሙ አንጋፋና በተለይም በውሃ ምህንድስና ዘርፍ ጠንካራ ምርምር የሚያደርግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአባይ ላይ ትልቅ ምሁራዊ ስራ ይጠብቀናል ብለዋል።

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከሉም ጎልብቶ ምሁራንና ተማሪዎች ለብሄራዊ ጥቅም ጉዳይ አበርክቷቸውን እንዲያሳድጉ ለማድረግ ዩኒቨርስቲው እገዛ ያደርጋል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.